...

The African Building Platform

Feature

ስለ መዘርዘር (Specification) አንዳንድ ነጥቦች

ውሂብ ከበደ
Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on telegram

Specification መዘርዘር ማለት ነው። እንዲሰራ፣እንዲገዛ፣እንዲገጠም የሚፈለግን ነገር በተሟላ ሁኔታ መግለጽን ያመለክታል። ሕንፃን በሚመለከት ከንድፍ ሥራው በተጨማሪ በጽሑፍ የሚሰጠውን መመሪያ ወይም የፍላጎት መግለጫ የሚያመለክት ነው።

ለሕንፃ ሥራ የሚውሉ በተለያየ ጊዜ የወጡ መደበኛ መዘርዝሮች አሉ። አብዛኛው የሕንፃ ሥራ መደቦች በእነዚህ መዘርዝሮች የተሸፈኑ ናቸው። ነገር ግን እንደ ሕንፃው ዓይነት ተጨማሪ መዘርዝሮችን ማከል አብዛኛውን ጊዜ ያስፈልጋል። በመደበኛ መዘርዝሮች ላይም ማስተካከያና ማሻሻያ ማድረግ የሚያስፈልግበት ጊዜ አለ።

ለሕንፃ ሥራ የሚያስፈልገውን የመዘርዝር ሰነድ የማዘጋጀት ኃላፊነት በዋናነት የአርኪቴክቱ ሲሆን ሌሎች መሐንዲሶችም ለየሚመለከታቸው መደብ መዘርዝሮች የማዘጋጀት ኃላፊነት አለባቸው።

መዘርዝር (Specification) ከሥራ መግለጫ (Bill description) ወይም የሥራ ዝርዝር (Bill of quantities) ጋር ያለውን ልዩነት ባለማጤን የሚፈጠር የግንዛቤ እጥረትና የስያሜ መምታታት አለ። አተገባበሩን በሚመለከት ለሕንፃ ሥራ የሚጠናቀረው ሰነድ የተለያየ ደረጃ አለው፤

  1. የተሟላ መዘርዝር ያልለው
  2. መደበኛውን መዘርዝር ብቻ የያዘ
  3. የመደበኛው መዘርዝር ስም ብቻ የተጠቀሰበት
  4. መዘርዝር የሌለው

የሰነዶቹ ዓይነት በአርኪቴክቱ ችሎታና በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች የሚወሰን እንደሆነ መረዳት ይቻላል። ለሙያ አገልግሎት የሚደረገው ክፍያ መጠንም ከነዚህ ምክንያቶች ውስጥ ጎልቶ ይወጣል። ባለድርሻ አካላት የሚባሉት አሠሪው ፣ አርኪቴክቱ እና ሥራ ተቋራጩ ናቸው።

ከአሰሪው የሚጠበቀው አርኪቴክት በሚመርጥበት ጊዜ በችሎታና በተመሰከረለት የሥራ ውጤት ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ማድረግ ነው። በተጨማሪም አርክቴክቱ በሕንፃ ሥራ ላይ ሙሉ ኃላፊነት እንዳለው መቀበል ይሆናል።

ከአርኪቴክቱ የሚጠበቀው ዲዛይን የሚያደርገውን እያንዳንዱን ሕንፃ በተለየ በመመልከት አግባብ ባለው ሁኔታ የተዘጋጀ መዘርዝር ማዘጋጀትና በግንባታ ወቅትም ሥራው በዚሁ መሰረት የተከናወነ መሆኑን ማረጋገጥ ነው።

ከሥራ ተቋራጩ የሚጠበቀው ሕንፃውን ለመገንባት የሚያቀርበው ዋጋ መዘርዝሩን በጥልቀት በማጥናት ተገቢ መሆኑን ማረጋገጥ ነው። የግንባታ እቃ አቅርቦትን በሚመለከትም አስተማማኝ የሆነ አሰራር መመስረት ነው።

በሕንፃ ሥራ ዋነኛው የዲዛይን ማቅረቢያ ንድፍ ነው ፤ ንድፍ ግን ብቻውን በቂ አይደለም ፣ በመዘርዝሮች መደገፍ አለበት። እንደየሀገሩ ሁኔታ የመዘርዝሮች አቀራረብ ይለያያል። ለምሳሌ የዩ.ኤስ. አሜሪካን ልምድ ካየን ንድፎቹ በጽሁፍ የተሞሉና ለፕሮጀክቱ በተለየ የሚያስፈልጉትን መዘርዝሮች የያዙ ናቸው።

በእኛ ሀገር ሁኔታ የንድፎች የጽሁፍ ይዘት እጅግ በጣም አነስተኛ ነው። ከመደበኛው የመዘርዝሮች ሰነድ ጋር የሚያያዙ ጠቋሚዎችም የሚመለከቱበት ሁኔታም የበዛ ነው። ይህም ከችሎታ ፣ ከትምህርት ሥርዐት ፣ ከሙያ ሥርዐትና ከክፍያ ጋር ይያያዛል። ይህም ሲባል ያደጉት ሀገሮች የዳበረ የአሠራር ልምድ ስላላቸው የምናየው የተሻለ ጎናቸውን ብቻ በመሆኑ እንጂ የተለያየ የጥራት ደረጃ እንዳለ መገመት አያዳግትም።

በኛም ሀገር አብዛኛው አቅርቦት በተጠቀሱት የችሎታ ፣ የትምህርት ሥርዐት ፣ የሙያ ሥርዐትና የሙያ አገልግሎት ክፍያ ምክንያት ዝቅ ያለ ቢሆንም ፤ ተፈላጊውን መረጃ ያሟላ የፕሮጀክት ሰነድ የሚያዘጋጁ የዲዛይን ቢሮዎችም አሉ። በእኔ ግምት በሚቀጥሉት አምስት አመታት ውስጥ በዚህ ረገድ ክፍተኛ መሻሻል እንደሚኖር የሚጠቁሙ አመልካቾች እየታዩ ነው።

የዲዛይን ቢሮ አደረጃጀት ላይ ማነቆ የሆኑ ጉዳዮች ከተፈቱና አርኪቴክቶች በሚሠሩባቸው ቢሮዎች የሙያ እድገት መሰላል ኖሮ ተረጋግተው ሙያቸውን እንዲያዳብሩ ከተደረገ አሁን የሚታየው የመሻሻል ምንጭ ይጎለብታል።

ለዚህም አስተዋጽዖ እንደሚያደርግ የሚጠበቀው አብዛኛዎቹን የዲዛይን ቢሮዎች ወደ የአንድ ሰው ቢሮነት እንዲያመሩ ምክንያት ከሆኑት አንዱ የሆነው የሙያ ምዝገባና የፈቃድ መስፈርት ላይ መሻሻል መታየቱ ነው። በዚሁ ዙሪያ የተደረጉ ጥናቶች እንዳሉ ይታወቃል። በተሳትፎ የታጀቡ እንዲሆኑና ተግባራዊ እንዲሆኑም ይጠበቃል።

Interesing article?

Check out the full journal for other interesting contents and more.

Thank you for reading Ketema, the African building platform.

Subscribe below to receive an email when a new issue is released.

Your email address will not be shared with anyone else, and it’s easy to opt out if you change your mind.

© October, 2024 Ketema Journal

Thank you for reading Ketema, the urban building platform.

Subscribe below to receive an email when a new bimonthly issue is published.

Your email address will not be shared with anyone else, and it’s easy to opt out if you change your mind.

Seraphinite AcceleratorOptimized by Seraphinite Accelerator
Turns on site high speed to be attractive for people and search engines.