...

The African Building Platform

Spotlight

ስለ ከተማ ፤ ቅፅ ፬

Medhanit Tadesse
መነፅር፤
Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on telegram

ስለ፡ ባቡር በአዲስ አበባ

የሰርኪስ ባቡር ተሰናክሎ ቆሞ ነበር። በቆመበት ቦታም ሰባራ ባቡር ተብሎ እስካሁን ድረስ ይጠራል። በዚህም ምክያት እንዲህ እየተባለ ይገጠም ነበር። ብነግርሽ ብነግርሽ አታጠናቅሪ፤
እንደ ሰርኪስ ባቡር ተገትረሽ ቅሪ።

ካየሁት ከሰማሁት፤
መርስዔ ኅዘን ወልደ ቂርቆስ

ስለ፡ ድልድይ

የራስ መኮንን ድልድይ መኪና በማሻገር የመጀመሪያው ድልድይ ሲሆን በድልድይነት ደግሞ ለአዲስ አበባ ሁለተኛው ነው፡፡ የመጀመሪያው የአድዋ ድልድይ ነው፡፡

ዝክረ አዲስ አበባ
ሰለሞን ማሞ ውቤ (ዶ/ር)

ስለ፡ የህዝብ ማጓጓዣ መኪና

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የህዝብ ማጓጓዣ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የተቋቋመው በ1935ዓ.ም ነው፡፡ የተጀመረውም ጣልያኖች ትተዋቸው በሄዱት አምስት አሮጌ የወታደር የጭነት መኪናዎች አማካኝነት ነበር፡፡

ዝክረ አዲስ አበባ
ሰለሞን ማሞ ውቤ (ዶ/ር)

ስለ፡ ትራፊክ መብራት

ከ1960ዓ.ም ጀምሮ የትራፊክ መብራት ወደ ኢትዮጵያ ገባ፡፡ (ይህም ማለት የትራፊክ መብራት መጠቀም ከጀመርን 53 አመታት ተቆጥርዋል።)

ዝክረ አዲስ አበባ
ሰለሞን ማሞ ውቤ (ዶ/ር)

ስለ : ትራፊክ ፖሊስ

የመጀመሪያዋ መኪና አዲስ አበባ ከገባች ከ25 ዓመታት በኃላ በካሳ ገብሬ አማካኝነት የአውቶሞቢል ዘበኛ ወይም የትራፊክ ፖሊስ ተመሰረተ፡፡ ከ15 ቀናት ትምህርታዊ ገለፃ በኃላ የትራፊክ ፓሊሶች ስራቸውን ጀመሩ፡፡

ዝክረ አዲስ አበባ
ሰለሞን ማሞ ውቤ (ዶ/ር)

ስለ፡ ከተማ ሰላም

በአዲስ አበባ ውስጥ የጠመንጃ ድምፅ መስማት የሚያጓጓ ነበር፡፡ በድንገት ባርቆ ወይም በሠርግ፣ ወይም ልጅ በመውለድ ደስታ ምክንያት የተተኮሰ እንደሆነ 37 ብር ተሩብ መቀጫ መክፈል ግዴታ ነበር፡፡

ይምጡ በዝና አዲስ አበባ
ያሬድ ገ/ሚካኤል

ስለ፡ አዳሪ ትምህርት ቤት

በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት የነበረው ምቾት አልጋው፣ ፍራሹ፣ ብርድልብሱ፣ ገላ መታጠቢያው፣ የነጭ ጤፍ እንጀራ እየተበላ ብርዝ እየተጠጣ ነበር፡፡

(ግሩም አሉ አባ አድማስ…አዳሪ ትምህርት ቤት እንዲህ ሲታወስ ያስገርማል)

ይምጡ በዝና አዲስ አበባ
ያሬድ ገ/ሚካኤል

ስለ፡ አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ በያመቱ የመስፋፋት ዕድል እያገኘች ስትሄድ፤ ጎጆ ቀልሶም ማከራየት ሲለመድ የየጠቅላይ ግዛቱ ነዋሪ ሕዝብም ከአለቃ እስከ ጭፍራው ድረስ አዲስ አበባን መጥቶ ለማየት ከፍ ያለ ወጭ የሚጠይቅ መሆኑን እየተገነዘበ ከመምጣቱ አስቀድሞ ገንዘብ አጠራቅሞ ነበር እንጂ ከፍ ያለ ድርጅት ሳያደርግ ወደ ከተማ የሚመጣ ሰው አልነበረም፡፡

(አሁን አዲስ አበባ ለመግባት ከአንደ ባላገር ሰው ምን ይጠበቅ ይሆን? ካለፈው ይቀል ወቅስ ይከብድ?)

ይምጡ በዝና አዲስ አበባ
ያሬድ ገ/ሚካኤል

Interesing article?

Check out the full journal for other interesting contents and more.

Thank you for reading Ketema, the African building platform.

Subscribe below to receive an email when a new issue is released.

Your email address will not be shared with anyone else, and it’s easy to opt out if you change your mind.

© October, 2024 Ketema Journal

Thank you for reading Ketema, the urban building platform.

Subscribe below to receive an email when a new bimonthly issue is published.

Your email address will not be shared with anyone else, and it’s easy to opt out if you change your mind.

Seraphinite AcceleratorOptimized by Seraphinite Accelerator
Turns on site high speed to be attractive for people and search engines.