The African Building Platform

Spotlight

መ ነ ፅ ር ፤

Menetsir is a platform born of the conviction that now, more than ever, it is necessary for us, Ethiopians, to explore our own local thinking, ideologies, philosophies, and ways of life. We explore our local books, music, literature, school of thoughts, and of cultural idioms on diverse topics.
Medhanit Tadesse
Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on telegram

ስለ፡ ከተማ አስተዳደር

ሥርዓት ከሌለው ሰፊ መንግሥት ይልቅ በሕግ የምትኖር ትንሽ ከተማ ሞያ ትሰራለች::

አጤ ምኒልክና ኢትዮጵያ
ነጋድራስ ገ/ሕይወት ባይከዳኝ

ስለ ፡ ከተማ

ከተማ እንደ ቦርሳ እኪስ አትከተት፣ እንደ ሃብል በአንገት ተጠልቃ በልብስ አትጋረድ፣እንደ ቡታንታ በሱሪ አትከለል ፣ እንደ ጀርባ ጋቢ አይጣልባት፡፡ ከተማን ያህል ነገር ገልቦ እያሳዩ ‘ተከናነብኩ’ ማለት ይከብዳል፡፡

የስንብት ቀለማት ፤ አዳም ረታ

ስለ ፡ ከተማና ቅርስ አጠባበቅ

በሀገራችን የዛፍ ወይም የሕንፃ ምስክርነት ለትውልድ ማቆየት የተለመደ ነው፡፡
ከዚህም የተነሳ ታላላቅ ዛፎች እንዳይቆረጡ ኮረብታዎች እንዳይፈርሱ ነባር የሕንፃ ቤቶች እንዳይደመሰሱ ጥንቃቄ ይደረጋል፡፡

ይምጡ በዝና ፤ አዲስ አበባ
ያሬድ ገ/ሚካኤል

ስለ ፡ ከተማና ጊዜ

ጥቂት ዓመታት ብዙ ነገር አፈራርሰውና ለዋውጠው ሲሄዱ ቅርቡን ጊዜ ድሮ ያስመስሉታል፡፡

የስንብት ቀለማት ፤ አዳም ረታ

ስለ ፡ ከተማና ገጠር ትስስር

የከተማው ኢኮኖሚ ለገጠሩ የገበያ ምንጭ ብቻ ሳይሆን የሠለጠነ የሰው ሃይልና የቴክኖሎጂ ዕድገት መሰረትም ነው፡፡

መንግሥትና የሕዝብ አስተዳደር
ነጋድራስ ገ/ሕይወት ባይከዳኝ

ስለ፡ ከተማና ቤት አሰራር

መደዳውን ሰልፍ ይዞ የተሰራ ነገር አያስጠላሽም፤
የማሕበር ወይም የቁጠባ ቤት አይደብርሽም ፤
አራት አራት ግድግዳ፡
አንድ አንድ መስኮት፡
ሁለት ሁለት መዝጊያ፡
ሁለት ሁለት ደረጃ፡
ሁለት ሁለት ክንፍ ዓይንሽን እስኪያምሽ ድረስ
ወደላይም ወደ ታችም የተደረደረ ፓኮ!
የማያባራ ሰልፍ…እኔ መቼም እዛ ውስጥ ኑር ቢሉኝ የማብድ ይመስለኛል፡፡

ካገር ፍቅር ፡ አዲ‘ሳባ
ጀሚል አክበር

ስለ፡ከተማ ውበትና ሰው

ከጎራው ዘልቄ እስኪ ልነጋገር
ካለሰው ቢወዱት ምን ያደርጋል አገር
የኔ ውብ ከተማ –
ሕንፃ መች ሆነና የድንጋይ ክምር፤
የኔ ውብ ከተማ –
መንገድ መች ሆነና የድንጋይ አጥር፤
የኔ ውብ ከተማ የኔ ውብ አገር
የሰው ልጅ ልብ ነው
የሌለው ዳርቻ የሌለው ድንበር፡፡
ሕንፃው ምን ቢረዝም፤ ምን ቢፀዳ ቤቱ
መንገዱ ቢሰፋ ቢንጣለል አስፋልቱ
ሰው ሰው ካልሸተተ ምንድን ነው ውበቱ;
እኔ ውብ የምለው
የሰውን ልብ ነው፡፡


ሱ!

ኦሮማይ ፤ በዓሉ ግርማ

ስለ፡ ከተሜ

ዘመናይ (ከተሜ) ሲያመሰግኑት እንጂ ሲወቅሱት አይወድም፡፡

መንግሥትና የሕዝብ አስተዳደር
ነጋድራስ ገ/ሕይወት ባይከዳኝ

Cover Feature

Interesing article?

Check out the full journal for other interesting contents and more.

Thank you for reading Ketema, the African building platform.

Subscribe below to receive an email when a new issue is released.

Your email address will not be shared with anyone else, and it’s easy to opt out if you change your mind.

© May, 2023 Ketema Journal

Thank you for reading Ketema, the urban building platform.

Subscribe below to receive an email when a new bimonthly issue is published.

Your email address will not be shared with anyone else, and it’s easy to opt out if you change your mind.