The African Building Platform

Spotlight

መ ነ ፅ ር ፤

Medhanit Tadesse
Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on telegram

ስለ፡ አዲስ አበባ

የአዲስ አበባን ከተማ ሲመሠርቱ አስቀድመው በእንጦጦ ጀመሩ፡፡ የዛሬው የአዲስ አበባ ከተማ ግን ጥንት ዝሆን የሚታደንበት በረሐ ነበር ይላሉ፡፡

መንግሥትና የሕዝብ አስተዳደር
ነጋድራስ ገ/ሕይወት ባይከዳኝ

ስለ ፡ ከተማ አሰፋፈር እና ቅርርብ

በአንድ ሀገር ውስጥ ዕውቀት (መሰረተ ልማት) ሲበዛ አምራቾች አይራራቁም፤ በየመንደሩ በየመንገዱ በየወረዳው ዕቃው ሁሉ አጠገብ ላጠገብ በያይነቱ ይሠራልና ለመለዋወጥ ሩቅ መንገድ መሄድ አያሳስባቸውም፡፡ ስለዚህም የተላላኪው ነጋዴ ዋጋ ይቀራልና የኑሮ ዋጋም ይረክሳል፡፡

መንግሥትና የሕዝብ አስተዳደር
ነጋድራስ ገ/ሕይወት ባይከዳኝ

ስለ ፡ ከተማ

ከተሞች የዕውቀት፤ የሃይማኖት፤ የፖለቲካ፤ በጠቅላላው የሰዎች ማህበራዊ ኑሮ መምሪያዎችና መገናኛዎች ሆነው መቆየታቸው ግልፅ ነው፡፡ የከተሞቹ ዕድሜም እየገፋ በሄደ ቁጥር ደግሞ ለዚያ አገር ሕዝብ የመልካም ታሪኩ መወደሻና መቀደሻ ስለሚሆኑ ከሌላው የውጭ ሕዝብ ጋር የሚያገናኙትና የሚያስተዋውቁነት ታሪካዊ ቅርሶቹ ይሆናሉ ፤ ናቸውም፡፡

አዲስ አበባ ትናገር
ታጀበ በየነ

ስለ ፡ ከተማና ጊዜ

የከተማዋን ታላቅነትና ዘመናዊነት በጉልሕ ከሚናገሩት ምስክሮች መካከል፤ በፕላን የተሰሩ መንገዶችና አደባባዮች፤ በሥርዓት የተሰሩ ቤቶች ሆቴል ቤቶችም ጭምር፤ የጥንት ቅርሳ ቅርሶች ማከማቻ ሙዚየሞች ከሌሎቹ ዝግጅቶች ጋር ተደራጅተው ሲገኙ ከተማዋ ታላቅ የሚለውን ስም ከማግኘተም በላይ፤ በሚቀርበው አገልግሎትም የልብ መናገር ያስችላል፡፡

ስለ፡ አዲስ አበባ ታሪክ

ከተማይቱ (አዲስ አበባ) ከተቆረቆረች አንስቶ፤ ሲታሰብ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ከተማ የመጡት የውጭ አገር መልዕክተኞች ከሞስኮ (ሩሲያ) ንጉሥ ከኒኮላስ ቄሣር የተላኩት
መልእክተኞች ነበሩ፡፡

አዲስ አበባ ትናገር
ታጀበ በየነ

ስለ፡ አዲስ አበባ

አዲስ አበባ ከተማ በ1968 ዓ.ም፡ ከአንድ ሚሊዮን ሕዝብ በላይ የሰፈረባት በ1,735 የዕድር ማህበሮች ውስጥ 235,000 ዕድርተኞች የሚኖሩባት፤ ከ65 ያላነሱ ኤምባሲዎች፤ከ16 ታላላቅ ዓለም አቀፍ የሰላም ድርጅቶች የሚገኙባት፤ከ16ሺህ ያላነሱ ልዩ ልዩ ነጋዴዎች የሚመላለሱባ፤የመንግስትና የግል የሆኑ ከሞተር ሳይክል እስከ ከባድ መኪና ተደምሮ ከ62 338 በላይ ተሽከርካራች የሚፈነጩባት 36 የክርስቲያን ፀሎት ቤቶችና ከ6 ያላነሱ መስጊዶች
የሚገኙባት፤ ታላቅ ከተማ ነበረች፡፡

አዲስ አበባ ትናገር
ታጀበ በየነ

ስለ፡አዲስ አበባ አና አፄ ምኒልክ

አ ፄ ምኒልክ በአዲስ አበባ በታኅሳስ 3 ቀን 1906 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አረፉ፤ አስከሬናቸውም ከ1906 እስከ 1909 ዓ.ም ድረስ መሞታቸው ሳይነገር በአዲስ አበባ ከተማ በስማቸው ግዛቱ
ይካሔድ እንደ ነበር ተፅፏል፡፡

አዲስ አበባ ትናገር
ታጀበ በየነ

ስለ፡ ከተማ ፣ ሰዉ እና ውበት

“ከተማዪን ካሳመራችሁ አይቀር እኔንም አሳምሩ።“

የስንብት ቀለማት
አዳም ረታ

Thank you for reading Ketema, the African building platform.

Subscribe below to receive an email when a new issue is released.

Your email address will not be shared with anyone else, and it’s easy to opt out if you change your mind.

© May, 2023 Ketema Journal

Thank you for reading Ketema, the urban building platform.

Subscribe below to receive an email when a new bimonthly issue is published.

Your email address will not be shared with anyone else, and it’s easy to opt out if you change your mind.