...

The African Building Platform

Updates

ስለ ከተማ ፤ ቅፅ ፫

Medhanit Tadesse
መነፅር፤
Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on telegram

#ስለ፡ ከተማና ኤሌክትሪክ መብራት

በዚህ ሰሞን ከማዘጋጃ ቤት ጀምሮ እስከ ራስ መኮንን ድልድይና ወደ አራዳ የሚወስደው ዋና መንገድ በኤሌክትሪክ መብራት ስለተበራ ማታ ማታ አላፊ አግዳሚውን ሁሉ ደስ አሰኝቶታል፤ እንደዚሁ ሆኖ የኤሌክትሪክ መብራት በከተማው ሁሉ ቢዘረጋ ከተማው እንዴት ባማረ ፤ ሌሊት ለሚጠብቁ ዘበኞችም በተመቸ ነበር፡፡ ይኸውም በቶሎ ይፈጸማል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡

ነሐሴ 7፣ 1920 ዓ.ም
ብርሀንና ሰላም ጋዜጣ ላይ የታተመ

#ስለ፡ ቤተ መንግስት ግብር አዳራሽ

ምኒልክ በዚሁ 1889 ዓ.ም. በስማቸውና በመልካቸው ብር አሳተሙ፤ በዚሁ ዓመት ከአውሮፓ መሐንዲሶች አስመጥተው ውስጡ አንድ፤ ውቅሩ ሦስት የሆነውን ታላቁን የግብር አዳራሽ በአዲስ አበባ ከተማ አስጀመሩ፡፡

አዲስ አበባ ትናገር
ታጀበ በየነ

#ስለ ፡ ከተማ

ማንኛዋም ከተማ የሰው ልጅ የስራ ውጤት ናት (እንስት ብትሆን)። እግዚር እንደ ተራራ ፣ እንደ ወንዝ ፣ እንደ ሎሚና እንደ ሰላጣ ፣ እንደ እግሮቻችንና እንደ ኪንታሮት አልስራትም ። የሰው ልጅ ያበጀት የክሱት ግብሩ ውጤት ብቻ ሳትሆን የድብቅ ነፍሱ ንቅናቄም ምልክት ናት። የሕልሙ ማህተም እንደ ማለት ::

የስንብት ቀለማት
አዳም ረታ

#ስለ ፡ ከተማና ትምህርት ቤት

ከተማዋ የመጀመሪያውን ት/ቤት ያየችው በ1889 ነበር። ዳግማዊ ምኒሊክ ትምህርት ቤት። ሁለተኛ ት/ቤቷን ለማየት ሀያ ስምንት አመት ፈጀቶባታል :: በ1917 የተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ተከፈተ። ሶስተኛው ት/ቤት ከጣሊያን መባረር በኋላ በ1934 የተቋቋመው የእቴጌ መነን
የሴቶች ትምህርት ቤት ነው፡፡

ትውልድ አይደናገር፥ እኛም እንናገር
አንዳርጋቸው ፅጌ

#ስለ : ከተማ ንድፍ

“አስፋልት ማልበሱ ቢያቅተንም እንዴት ጠጠሮች የለበሱ በዘመናዊ መንገድ የተቀየሱ የከተማ መንገዶች እንዲኖረን ማድረግ ያቅተናል? እንዴት ከድንጋይና ከሲሚንቶ ለሚሰራ የማንም መንግስት በየሃገሩ በቀላሉ የሚቆልለውን የህንጻ ና የቤት ግንባታ ያቅተናል? እንዴት በዚህ ዘመን ሰዉ በየመንደሩ የሽንት ቤት ና የቆሻሻ ውሃ በቤቱ መሃል እየፈሰሰ ተኝቶ የሚያድርበት ሁኔታ ዝም
ተብሎ ይታያል? “

ትውልድ አይደናገር፥ እኛም እንናገር
አንዳርጋቸው ፅጌ

#ስለ፡ ከተማና ድንቁርና

የምትወልድን ሴት ይሁን፣ የታመመን ሰዉ ለህክምና ሃኪም ቤት ማስተኛት የማይችል ማህበረሰብ ነው፡፡ እናት ልጇን አምጣ ከወለደች በኋላ ምጧ የማያቆምበት ከተማ፣ አዲስ አበባ ነበረች። እንዲህ አይነት ከተማ መሆኗን ሳያውቁ ተወልደው አድገው ሰዎች የሚሞቱባትም
ከተማ፣ አዲስ አበባ ነበረች።

ትውልድ አይደናገር፥ እኛም እንናገር
አንዳርጋቸው ፅጌ

#ስለ፡ከተማ

እንዴት ይች የኔ ከተማ ትልቅ
ማድቤት ሆና ቀረች?

ትውልድ አይደናገር፥ እኛም እንናገር
አንዳርጋቸው ፅጌ

#ስለ፡ አዲስ አበባ እና አራዳ

ወይ አዲስ አበባ፤ ወይ አራዳ ሆይ፤
አገርም እንደ ሰው ይናፍቃል ወይ!

Interesing article?

Check out the full journal for other interesting contents and more.

Thank you for reading Ketema, the African building platform.

Subscribe below to receive an email when a new issue is released.

Your email address will not be shared with anyone else, and it’s easy to opt out if you change your mind.

© October, 2024 Ketema Journal

Thank you for reading Ketema, the urban building platform.

Subscribe below to receive an email when a new bimonthly issue is published.

Your email address will not be shared with anyone else, and it’s easy to opt out if you change your mind.

Seraphinite AcceleratorOptimized by Seraphinite Accelerator
Turns on site high speed to be attractive for people and search engines.